=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
በምድርም ሆነ በነፍሶቻችሁ ላይ ምንም መከራ አይገጥማችሁም። ከመከሰቱ በፊት በመፅሐፍ ውስጥ የተፃፈ ቢሆን እንጂ። ብዕሩ ደርቇል ፣ መዝገቡም ተነስቷል ፣ ጉዳዩም ተፈፀመ ፤ ውሳኔዎችም ሁሉ ተፅፈዋል ፤ አሏህ የፃፈልን እንጂ አይነካንም። የሳተህ ነገር አያገኝህም ነበር ያገኘህም አይስትህም ነበር።
ይህ እምነት በነፍስህ ውስጥ ከፀና እና በህሊናህ ውስጥ ከተደላደለ መከራዎች ሁሉ ስጦታ ፣ ፈተናዎች ሁሉ ሽልማቶችና ኒሻኖች ይሆኑልሃል። አሏህ ኸይር ያሻለትን ሰው ይፈትነዋል። ታመምኩ ፣ ልጄ ሞተ ብለህ አትጨነቅ። ከሰርኩ ፣ ቤቴ ተቃጠለ ብለህም አትረበሽ። ፈጣሪህ ወስኗል ፤ ውሳኔውም ተፈፀመ። ምርጫውም እንዲህ ነው። የሚሻለውም አሏህ የመረጠው ነው። ምንዳውም ተገኘ ፤ ወንጀሉም ተማረ። የምስራች መከራ ለደረሰባቸው ሰዎች....... መታገሳቸው እና ሰጭና ተቀባይ ፣ ሰብሳቢ ፣ የሚዘረጋና ስለሚሰራው የማይጠይቅ ፍጡሮቹ ግን የሚጠይቁ የሆነው ጌታቸው የመረጠላቸውን በደስታ በመቀበላቸው ደስ ይበላቸው።
ህሊናህ አያርፍም ፤ ነፍስህም አትረጋም ፤ የልብህ ጉትጎታም አይሰክንም በቀዷና በቀድር እስካላመንክ ድረስ። የምታገኘውንና የሚያጋጥምህን ሁሉ የተፃፈበት የቀድር ብዕር ደረቀ ፤ ስለዚህ በቁጭት ራስህን አትጉዳ። ግድግዳው እንዳይፈርስ መከላከል እችል ነበር ብለህ አታስብ። ውሃው እንዳይፈስ ፣ ነፋስም እንዳይነፍስ ፣ ብርጭቆውም እንዳይሰበር መከላከል ትችል እንደነበር እራስህን አትሸንግል። ይሄ ብፈልግም ብትፈልግም ፣ ባልፈልግም ባትፈልግም ከቁጥጥራችን ውጭ ነው። የተወሰነው ነገር ይከሰታል ፤ የተፃፈውም ተግባራዊ ይሆናል።
አል-ቁርአን 18:29
«የሻም ሰው ይመን የሻም ይካድ»
የቁጣ ፣ የዋይታና ራስን የመውቀስ ወታደሮች ሳይከቡህ በፊት ለቀድር እጅህን ስጥ። የቁጭት ጎርፍ ሳያጥለቀልቅህ በፊት ለቀድር እውቅና ስጥ። ስለዚህ ነገሮች እንዲሳኩልህ ምክኒያቶቹን ከፈፀምክና ዘዴዎችን ከተጠቀምክ በኋላ ግን ደግም ትጠነቀቀው የነበረውን ነገር ቢመጣብህ መሆን የነበረበትና መከሰት የነበረበት እሱ ነውና ራስህን አረጋጋ። «እኔኮ እንዲህና እንዲህ ባደርግ እንዲህና እንዲህ ይሆን ነበር» አትበል ፤ ባይሆን «አሏህ ወሰነ ያሻውንም ፈፀመ» በል።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|